Message/ የተቀባ ቃል

ሀሰተኛ ነብይ ~ ብዙ ሰው ስለተከተለው ትክክለኛ አይሆንም

ብዙ ሰዎች እንዴት እገሌ ሀሰተኛ  ነብይ ወይም አስተማሪ ከሆነ ይህ ሁሉ ሰው ይከተለዋል ? ይላሉ ፣ ለማመንም ይቸገራሉ።

“ጥምብ ባለበት አሞራ ይሰበሰባል” የሚባል ተረት አለ ።  ለኔ የዚሀ አይነት ነገር ነው የሚታየኝ  ባብዛኛው በነዚህ ሰዎች ዙሪያ የሚሰበሰቡ ሰዎች ወይ የዋሆች ፣  የጌታን ቃል ጠንቀቀው የማያውቁ  አለያም የሆነ የሚበላ ነገር የሚፈልጉ ናቸው።

የሀሰተኛ አስተማሪዎች ዋና መገለጫቸው ድፍረታቸውና ተከታዮቻቸውን የሚይዙበት የሰነልቦና ጨዋታ ነው ።. ለምሳሌ የብልጽግና ወንጌል ሰባኪዎች ገንዘብን በሚፈልጉና በደሆች ዘንድ ተሰሚነት አላቸው።. የመጽሀፉን ቃል በማጣመም ሁሉ እንደሚሳካና ቤታቸው ዘንድ እንደሚመጣ አነቃቂ በሆነ መንገድ ይነግሯቸዋል ፣. ለማመን እስኪገርም ሰዎች አቅላቸውን ስተው ይከተልዋቸዋል.

ሌላኛዎችሁ ቤታቸውን የሚያጣብቡት የታመሙና መፍትሄ የቸገራቸው አማኞች ናቸው ። እነዚህ ሰዎች  ጌታ  በነሱ በኩል ብቻ እንደሆነ የሚሰራው በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ ሰለሚናገሩ የቸገረው አማኝ በተለይ አሁን ኢትዮጵያ ወስጥ ካርቶን እያነጠፈ በጠሎት ቤታቸው ያድራል ይውላል ፣ ብዙ ህዝብ በስቴድየምና አዳራሽ ይኮለኮላል። ይህንን የሚያዩ የዋሆች ይህን ያክል ህዝብ እየተከተላቸው እንዴት ሀሰተኛ ይሆናሉ ይላል።.

በዚህ ጉዳይ ላይ ከጌታ ቃል ትንሽ ምሳሌ ልስጥ ። በመጽሐፍ ቅዱሰ ዘመን ቴዎዳስ የሚባል ሰው ተነስቶ ነበር። ይህ ሰው የተላከ ነው፣ ነጻ ያወጣናል በሚል በዛ ዘመን የህዝብ ቁጥር 400 ሰው ተከትሎት ነበር፡፡ ይህ ቁጠር ብዙ ነው ፡ ዛሬ ባለ ግምት ከ 4.000 ~ 400.000 + ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ሰው ይህን ያህል ሰው ቢከተለውም ትክክለኛ አልነበረም፡፡ እሱም ጠፋ የተከተሉትም  ተበተኑ፡፡

       ነገር ግን በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የከበረ የሕግ መምህር ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ በሸንጎ ተነሥቶ ሐዋርያት ጥቂት       ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ፥ እንዲህም አላቸው፦ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ስለ እነዚህ ሰዎች ምን እንደምታደርጉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከዚህ ወራት አስቀድሞ ቴዎዳስ፦ እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ ተነሥቶ ነበርና፥ አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎችም ከእርሱ ጋር ተባበሩ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበተኑ እንደ ምናምንም ሆኑ ከዚህ በኋላ ሰዎች በተጻፉበት ዘመን የገሊላው ይሁዳ ተነሣ ብዙ ሰዎችንም አሸፍቶ አስከተለ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበታተኑ።   (ሐዋ 534~38)

በጲላጦስ የአገዛዝ ዘመን በርባን የተባለ አንድ ህዝብ ያስቸገረ ሌባና ወንበዴ ነበር ። ይህ ሰው ታሰሮ ከሀዝቡ ተገልሎ ነበር ፣ ይሁን እንጂ ኢየሱስ በአገልግሎቱ ምክንያት ተይዞ ለፈርድ ሲቀርብ  ጲላጦስ የዚሀን ሰው ጉዳይ ለድርድር አቀረበው።  በወቅቱ የነበሩት ካሀናትም ወንበዴውን በርባን ሰዎች እንዲቀበሉት ዘመቻ አካሄዱ።  ጲላጦስም ለሀዝቡ ጥያቄ አቀረበላቸው ፣ ማንን ልፈታላችሁ ትወዳላቸሁ፟?

     ጲላጦስም፥ የካህናትን አለቆችና መኳንንትን ሕዝቡንም በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦
ሕዝቡን ያጣምማል ብላችሁ ይህን ሰው ወደ እኔ አመጣችሁት፤ እነሆም፥ በፊታችሁ መርምሬ ከምትከሱበት ነገር አንድ     በደል ስንኳ በዚህ ሰው አላገኘሁበትም።
ሄሮድስም ደግሞ ምንም አላገኘም፤ ወደ እኛ መልሶታልና፤ እነሆም፥ ለሞት የሚያደርሰው ምንም አላደረገም፤
እንግዲያስ ቀጥቼ እፈታዋለሁ። በበዓሉ አንድ ይፈታላቸው ዘንድ ግድ ነበረና።
ሁላቸውም በአንድነት፦ ይህን አስወግድ፥ በርባንንም ፍታልን እያሉ ጮኹ፤
እርሱም ሁከትን በከተማ አንሥቶ ሰውን ስለ ገደለ በወኅኒ ታስሮ ነበር።
ጲላጦስም ኢየሱስን ሊፈታ ወድዶ ዳግመኛ ተናገራቸው፤
ነገር ግን እነርሱ፦ ስቀለው ስቀለው እያሉ ይጮኹ ነበር።
ሦስተኛም፦ ምን ነው? ያደረገውስ ክፋት ምንድር ነው? ለሞት የሚያደርሰው በደል አላገኘሁበትም፤ ስለዚህ ቀጥቼ እፈታዋለሁ አላቸው።
እነርሱ ግን እንዲሰቀል በታላቅ ድምፅ አጽንተው ለመኑት። የእነርሱ ጩኸትና የካህናት አለቆችም ቃል በረታ።
ጲላጦስም ልመናቸው እንዲሆንላቸው ፈረደበት።
ያንን የለመኑትንም፥ ስለ ሁከት ሰውንም ስለ መግደል በወኅኒ ታስሮ የነበረውን አስፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው     ሉቃ 23. 18-25

በርባን በጣም ብዙ ህዝብ ነው የጮኸለት ፣ ብዙ ህዝብ ነው እንዲፈታ የደገፈው፣ የሃይማኖት መሪዎቹ ሳይቀር በማስታወቂያ ህዝቡ እንዲቀበለው ነው የሰሩት ። ይህንን ያሀል ሰው በርባን ይፈታልን ብሉ ቢጮህም ፣  የፈለገ ማስታወቂያ ቢሰራለትም በርባን ግን ሌባና ነፍሰ ገዳይ ነበር ። የሀዝቡ ደጋፍ የበርባንን ንጽህና አያረጋገጥም.

የአገልጋይ ትክክለኛነት ማረጋገጫው የትምህርቱ ትክክለኛነት፥ የልምምዱና የአገልግሎቱ መሰረት የጌታ ቃልና ትክክለኛው ወንጌል መሆኑ ነው እንጂ የሚከተለው ሰው ብዛት አይደለም ። ተባረኩ